Ethiopia: ለፖለቲካ ትርፍ ሲባል ታሪክ የደበቃቸው የቀዳማዊ ኃ/ስላሴ ወላጅ እናት ማን ናቸው ? The Real Mother Of Haile Selassie

author Andafta   1 год. назад
220,777 views

935 Like   210 Dislike

Ethiopia: ስለ አፄ ምኒልክ ገዳይ እና አሟሟት ያልተሰማ አስገራሚ ታሪክ

ልዑል ኤርሚያስ ስለ አያቱ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ያልተሰሙ ነገሮች

ETHIOPIA የምኒልክ ቤተመንግስት ሴራና የሃያ ደቂቃው ቀውጢ

የ1969 ጥር ወር ብዙ ውጥረት የነበረባት ወር ነች:: በተለይ ለላይኛው ቤተ መንግስት የደርግ አባላቱን እንደ ንፊፊት ወጥሮ ካሁን አሁን ይፈነዳል ተብሎ የሚጠበቅ:ከተራ ታጣቂው አንስቶ እስከ ሹማምንቱ ድረስ የታጠቀውን የነብስ ወከፍ መሳሪያ አቀባብሎ ጠቋሚ ጣቱን ከምላጩ ላይ ጣል እንዲያደርግና ኮሽ ባለ ቁጥር ካሁን አሁን ተጀመረ እየተባለ የሚያስበረግግ ወር:: የኢትዮጵያ አብዮት ከፈነዳበትና ከመስከረም 2 የመንግስት ለውጥ አንስቶ ጥር 26 1969 በያኔው ሻለቃ መንግስቱ የሚመራው ቡድን በአሸናፊነት እስከወጣበት ቀን ድረስ ሃገሪቷ አንድ መሪ አልነበራትም:: ይህች ጥር 26 ቀን ግን ስልጣን መጋረጃዋን ለሻለቃ መንግስቱ ወለል አድርጋ የከፈተችላቸው ቀን ሆነች:: +++ቅድመ ታሪክ+++ (ከየካቲት 1966 እስከ መስከረም 2 1967) ከክርስቶስ ልደት በፊት ጀምሮ እስከ ሃያኛው ክፍለዘመን ኢትዮጵያን ሲገዛ የነበረው ዘውዳዊው ስርአት በየካቲቱ አብዮት ተገርስሶ ግብአተ መሬቱ ሆነ:: የንግስተ ንግስት ዘውዲቱን ሞት ተከትለው ዙፋኑ ላይ ጉብ ያሉት ቀዳማዊ ሃይለስላሴ ገና ስልጣን ከመያዛቸው “የልጅ እያሱን ስልጣን በመንጠቅ”ሴረኝነት ቀጥሎም በጣልያን ወረራ ምክንያት ወደ እንግሊዝ ሃገር በመሰደዳቸው በኮብላይነት ከዛም በኋላ ጀግናው በላይ ዘለቀን በስቅላት በመቅጣታቸው በጨካኝነት ሲወቀሱ የኖሩ ናቸው:: ከአርባ አመታት በላይ የያዙትን ስልጣንም ለአልጋ ወራሻቸውና ለሌሎች ሹማምንት ለማጋራት ስላልፈለጉ በስልጣን ወዳድነታቸውም ውስጥ ውስጡን ሲወቀሱ ኖረዋል:: በ1953 ዓመተ ምህረት በታህሳስ ወር በተለይ ወንድማማቾቹ መንግስቱ ነዋይና ገርማሜ ንዋይ ሞክረውት የከሸፈው መፈንቅለ መንግስት የንጉሱን ዙፋን መነቅነቅ እንደሚቻል ያመለከተና ንጉሱ ብዙ ተቃዋሚዎችን ከውስጥም ከውጭም ማፍራታቸውን ያሳየ ጉዳይ ሆነና አለፈ:: በ1960 ዎቹ አጋማሽ አመታት በከተማ ውስጥ እየናረ የመጣው የኑሮ ውድነትና በንጉሰ ነገስቱ በጎ ፍቃድ በብዛት ወደ ውጭ ሃገር ተምረው የመጡ ምሁራን ቁጥራቸው ከምንግዜውም በበለጠ መበራከትአንድ ሲሆን በተለያዩ ቡድኖችና ስብስቦች የንጉሱን ስርአት መውቀስ ወረቀቶችን ማተምና ማሰራጨት በየጉባኤው ተነስተው እና ተነክተው የማያውቁ ጥያቄዎችን ማንሳትና መጠየቅ ተጀመረ:: በዚሁ በ1960 ዎቹ አጋማሽ የንጉሰ ነገስቱ መንግስት ድንገተኛ የነዳጅና የአንዳንድ ሸቀጦችን የዋጋ ጭማሪ ይፋ ሲያደርግ ግን ውስጥ ውስጡን ሲብላላ የነበረው የህዝቡ ብሶት ገነፈለና ወደ አደባባይ መፍሰስ ጀመረ:: የየካቲት ወር የተቃውሞ ሰልፍም የተለያዩ ማህበራትን በየፈርጅ በየፈርጃቸው አሰባስቦ የቡድን ጥያቄዎችን ወደ ንጉሱ እንዲያቀርቡ ሲያደርግ የወታደሮችም ቡድን “ደርግ” የሚል ስያሜ ይዞና ጡረተኛውን ጀነራል አማን ሚካኤል አንዶምን በሊቀ መንበር ጋብዞ ጥያቄዎችን ለንጉሰ ነገስቱ በ“ፍጹም ታዛዥነት” ሲያቀርብ ቆየ:: “ጃኖ ሆይ እባክዎ አከሌን ከስልጣኑ ያውርዱልን”እያሉ ጥያቄያቸውን ያቀርባሉ እርሳቸውም “ይሁን” ይላሉ:: “ጃኖሆይ አከሌን ይሹሙልን” ይላሉ ::ጃኖሆይም “እሺ” ይላሉ::ይሄ ሁሉ ሲሆን ደርጎቹ ውስጥ ውስጡን ስራቸውን እየሰሩ ነበር:: በንጉሰ ነገስቱ ዙሪያ የነበሩትን የደህንነትና የጸጥታ መዋቅሮች ገዝግዘው ገዝግዘው ጫፏ ስትቀር መስከረም ሁለት ቀን “ጃኖሆይ ለእርሶ ደህንነት ወደሚመች ቦታ እባክዎ አብረውን ይሂዱ”ብለው ወደ አራተኛ ክፍለ ጦር ወሰዷቸውና ደርግ በይፋ በመስከረም ሁለት ስልጣኑን ያዘ:: በዚህም ጡረተኛው የንጉሱ ጀነራል አማን ሚካኤል አንዶም ሊቀ መንበር:ሻለቃ መንግስቱ ሃይለማርያም ተቀዳሚ ሊቀ መንበር ኮሎኔል አጥናፉ አባተ ምክትል ሊቀ መንበር ሆነው ተመረጡ:: (እስከ ህዳር 13 ቀን 1967) ወታደራዊው መንግስት ስልጣን ከመያዙ ቀድሞ እውቅ ምሁራን ታላላቅ ጸሃፍትና የፖለቲካ ተንታኞች ደርግ ስልጣኑን መያዙ አስፈላጊ እንደሆነና ሃገር የመምራት ሃላፊነትን መቀበል እንዳለበት ሲያቀነቅኑ: አንዳንዶች ደግሞ (እንደ እንግሊዝ)ዘውዱ የአንድነት ምልክት ሆኖ ህገመንግስታዊ ጠቅላይ ሚኒስቴር እንዲሾም የተቻላቸውን ቅስቀሳ ሲያደርጉ ቆዩ::ሆኖም ግን በአቋራጭ የደርግ ስልጣን መያዝ ግን እምብዛም የጎረበጠውና ያጉተመተመው ከንጉሱ ደጋፊዎች ውጪ ነበር ማለት አያስደፍርም:: በዚያች በተረገመች በህዳር 13 ቀን 1967 በዛች ታሪክን ባዳፈነች እለት የደርግ የጭቃ ጅራፍ መተርተር ሲጀምር ግን መስከን የጀመረው የለውጥ ምንጭ ደፈረሰ:: ደርግ በአንድ ምሽት የራሱን ጥቂት አባላትና የገዛ ሊቀ መንበር ጀነራሉን ጨምሮ ስልሳ ሹማንቶችን ዛሬ የአፍሪካ ህብረት የተሰራበት ወህኒ ቤት ውስጥ በመትረየስ ጠመንጃ ረፈረፋቸው:: (ከህዳር 13 በኋላ…) ደርግ ውስጡ ያለው ባህርይ እየተገለጠ ወጣ:: የወታደር ጀብደኝነት እንጂ የሃገር መሪነት ብስለት እንጥፍጣፊዋም እንኳን ያልነበረባቸው አብዛኛዎቹ አባላት የኤርትራን ጉዳይ በተባበሩት መንግስታት አዳራሽ ሽንጣቸውን ገትረው በመከራከርና የአፍሪካ አንድነትን እውን ከማድረግ ጀምረው ዋና ጽህፈት ቤቱን አዲስ አበባ ላይ እንዲቆም ታላቅ ጀብድ የፈጸሙትን ጸሃፊ ትእዛዝ አክሊሉ ሃብተወልድን ከወንድማቸው ከአካለወርቅ ሃብተወልድ ጋር እንደ ዶሮ በአንድ ካቴና ግራና ቀኝ እጃቸውን አቆራኝተው መግደላቸው እንኳን ሊጸጽታቸው ቀርቶ በመግደላቸው ይፎክሩና ያቅራሩ ጀመር::በየምሽቱ የግድያ አዋጅ ጀርባም የይርጋ ዱባለ “የፍየል ወጠጤ”ቀረርቶን ህዝቡ መስማት የእለት ተእለት ስራው ሆነ:: ደርጎች ስልጣን እራሳቸው መያዛቸው ሊያስከትል የሚችለውን ጉዳት ጠንቅቀው አውቀውታል:: በቅድሚያ በአብዛኛው ህዝብና በጦሩ ዘንድ ያን ያክል እውቅና የለንም ብለው ስላሰቡና አብዛኛዎቹ በሰላሳዎቹ መጀመሪያ እድሜ ላይ ይገኙ የነበሩ አፍላዎች ስለነበሩ በእድሜም በአመራርም ብስለት ያለውን ሰው ሲያፈላልጉ ቆይተው ዝምተኛውንና የኦሮሞ ተወላጁን ጀነራል ተፈሪ በንቲን አገኙና በአብዛኛው ድምጽ ድጋፍ ሊቀ መንበራቸው አደረጓቸው:: እንግዲህ በአንዳንድ ጸሃፍት የሚነገረውና ጓድ መንግስቱ ሃይለማርያም ከመንግስት ለውጥ (ከመስከረም 2 1967) ጀምሮ ስልጣን ያዙ እየተባለ የሚወራው አደናጋሪ ጽሁፍ ፍጹም ሃሰት ነው::በእርግጥ ከመጋረጃው ጀርባ በመሆን አድራጊና ፈጣሪ ፈላጭና ቆራጭ እንደነበሩ አብዛኛዎቹን ያስማማል:: ቀደም ብለን እንዳየነው ደርጎች ሊቀመንበር ከራሳቸው አባል ለመምረጥ ያልፈለጉት በህዝብ ዘንድ እውቅና የለንም ብለው ነበር::ከጀነራል አማን ግድያ በኋላ ለሊቀመንበርነት እጩዎች በሚቀርቡበት ግዜ አንዳንድ የደርግ አባላት “ለምን ከራሳችን አባሎች አንመርጥም ? በተለይ ሻለቃ መንግስቱ ሊቀመንበር እራስዎ ይምሩን” የሚል ሃሳብ ቀርቦ እንደነበር ነገር ግን “መንግስቱ ለስልጣን ብለው ነው አማንን ያስገደሉት” የሚለው ሃሜታ እንዳይስፋፋ ሳይሰጉ አይቀርም ይላሉ ሌተና ኮሎኔል ፍስሃ ደስታ የደርጉ ምክትል ፕሬዚደንት ምስክርነታቸውን ሲሰጡ:: ደርግ ከሊቀመንበር አማን ሚካኤል አንዶም በኋላ ሶስት እጩዎችን ለምርጫ አቀረበ::እነርሱም ከምድር ጦር ከባህር ሃይልና ከአየር ሃይል ነበሩ::ከአየር ሃይል እጩ የሆኑት ዝነኛው የጦር ጀት አብራሪ ኮሎኔል አምሃ ደስታ:ከባህር ሃይል ደግሞ ዋና አዛዡ ኮሞዶር ጣሰው ደስታ ሲሆኑ ከምድር ጦር ደግሞ ብርጋዴር ጀነራል ተፈሪ በንቲ ነበሩ::እዚህ ጋር የወታደሩን ደካማና ጠንካራ ጎን አብጠርጥረው የሚያውቁት ሻለቃ መንግስቱ ጀነራል ተፈሪ እንዲመረጡ ካላቸው ጽኑ ፍላጎት የተነሳ ሰውዬውን በእጩነት አቅርበው ስለጀነራሉ ግለ ታሪክ ሲነገር እጅግ ባማሩ ቃላት አሸበራርቀው የመራጮቹን የደርግ አባላት ቀልብ ሲይዙ እንደነበረ በወቅቱ አባል የነበሩ ደርጎች መስክረዋል:: ያም ተባለ ይህ በጭምተኝነታቸው የሚታወቁትና የሁለተኛ ክፍለ ጦር አዛዡ የሸዋ ኦሮሞው ተፈሪ በንቲ ከጀነራል አማን አንዶም ጋር ሲነጻጸሩ ተለሳላሽ ጸባይ ያላቸው እነ መንግስቱ ሃይለማርያም የሚያደርጉትንም የስልጣን መሽሎክሎክ ይገታሉ ተብለው የማይታመኑ ሰው ከመሆናቸው የተነሳ ሳይሆን አይቀርም በእነ መንግስቱ እጩ አቅራቢነት የተመረጡት:: ከዚህ የሊቀመንበር ምርጫ በኋላ ምን ሆነ?የደርጉ ቋሚ ኮሚቴ አባላትስ እነማን ነበሩ?ሚናቸውስ ምን ነበር?እርስ በራስ ያላቸውስ ግንኙነት ምን ይመስል ነበር? ይቀጥላል……. DireTube

"ጥፍርን በፒንሳ" የ ኮሜዲያን እሸቱ አዲስ ቀልድ "የት ነበርን? " 01 Yet neberin? -01 Comedian Eshetu Melese new c...

Best stundup comedy show. comedian eshetu melese. yet neberine, zemenefiseha, melemelawin. Best stundup comedy show. comedian eshetu melese. yet neberine, zemenefiseha, melemelawin የት ነበርን \ \ ስታንዳፕ ኮሜዲ \ ለገና በአል በኢቲቪ የቀረበ \ የበአል ኮሜዲ \ ኮሜዲያን እሸቱ መለሰ \ አዲስ የአማርኛ ስታንዳፕ ኮሜዲ \ ክበበው ገዳ \ ፍልፍሉ\ ልጅ ያሬድ \ ፓስተር ቶማስ \ አዲስ ኮሜዲ \ ምርጥ ኮሜዲ\ አዲስ አማርኛ ፊልም\ ዶ/ር አብይ አህመድ / ዜና\ \ ኢሳት Yet neberin? standup comedy \ Gena holiday show on Etv meznagna \ holiday comedy \ comedian eshetu melese new \ Amharic standup comedy \ kibebew geda \ filfilu \ dereje haile \ tesfaye kassa \ lij yared \ paster Thomas \ Traver Noah \ Kevin heart \ Cris rock \ eddy murphy \ new Amharic film \ new Amharic standup comedy \ best Standup comedy \ the daily show \ top 10 best comedian in the world.

ATV: ዝርርብ ምስ ኣቶ ዓብደላ ኣደም ብዛዕባ እዋናዊ ጉዳያት ኤርትራ - Part 1 - 17 Jan, 2019

ATV - ኣሰና ቴለቪዥን፡ ብ ወለንታዊ ደገፍ ግዱሳት ኤርትራውያን ናብ ኤርትራን ከባቢኣን ብሳተላይት ን 24 ሰዓታት ዝመሓላለፍ፡ ነጻ ኣገልግሎት ቴለቪዥን ኤርትራውያን እዩ። SUBSCRIBE TO ATV: https://www.youtube.com/watch?v=0ybSKwUVChg

Comments for video: